Property Tips

በአሁን ፀአት ቤትን ለኪራይ ገቢ ብሎ መግዛት አዋጭ Investment ነው?

January 20, 2026
245 views

ቤት ለኪራይ ገቢ ብሎ መግዛቱ የሚለው ሃሳብ በራሱ አዋጪነት አለው። ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገንዘብ በገቢ በኩል የአብዛኛውን ሰው ያለበትን

የህይወት ወጪዎች ለመሸፈን እና ከቤቱ ግዥ ጋር የተገናኙ የባንክ ብድሮችን ካሉበት ለመክፈል ይረዳል።

ነገር ግን ቤቱን የመግዛት ምርጫ ላይ ጥንቃቄ ይፈልጋል። ምክንያቱም አብዛኛውን ግዜ አዲስ አበባ ውስጥ ለኪራይ ተመራጭነት

ያላቸው ቤቶች አካባቤያቸው አማራጭ መንገዶች ፣ የገበያ ማእከሎች ፣ ሆቴሎች ፣ ሆስፒታሎች ፣ ህግ አስከባሪ አካላት ፣ ስፋት ያለው የእሳት አደጋ

መኪና የሚያስገባ የውስጥ መንገድ ፣ የልጆች መጫዎቻዎች እና መዝናኛዎች ያላቸው ናቸው። እዚህ ጋር ልብ እድትሉ የምፈልገው አዲስ አበባ ውስጥ የቤቶች የኪራይ ዋጋ በወር ከ20 ሺ እስከ 300 ሺ እና ከዛ በላይ ይደርሳል። ይሄንን ከኪራይ ዋጋ ልዩነት እያመጣ ያለው ከፍተኛውን የኪራይ ዋጋ እየያዙ ያሉ ቤቶችን ያሉበት አካባቤ በብዛት የውጭ ድርጅቶች ፣ ኤንባሲዎች ፣ እና ለአየር መንገዱ ከቅርብ እርቀት ላይ መገኘታቸው ነው።ስለዚህ ከግብይታቹ በፊት እነዚህ ነገሮች የምታያቸው ቤቶች ሟሟላታቸውን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል።

ሁሉም ሰፈር የራሱ የሆነ ገቢ ቢኖረውም ከሁሉም ሰፈር የምናገኘው የኪራይ ገቢ ግን የተለያየ ነው።


የቤቶችን የኪራይ ዋጋ እየተመነ ያለው ምንድነው?

ለከተማ እና ለህዝብ መጓጓዣ ቅርብ በሆኑ ማዕከላዊ ቦታዎች ውስጥ የኪራይ መጠን ከፍ ያለ ይሆናል። በአንጻሩ ከመሃል ከተማ ርቀት ያላቸው አካባቢዎች ከበፊቱ ጋር ሲወዳደር በመጠኑ ዝቅተኛ የኪራይ ዋጋ ይኖራቸዋል። ሰፋ ያለ ካሬ ላይ ያረፉ ቤቶች ከፍተኛ ወርሃዊ የኪራይ ዋጋዎችን ይጠይቃሉ። ከዚህም በተጨማሪ ዘመናቸውን የጠበቁ የኪችን/ የመታጠቢያ ፣ የልብስ ማጠቢያ እና ሌሎች መገልገያዎች ያሉዋቸው እና ጥበቃ ከመኪና ማቆሚያ ጋር ያላቸው ቤቶች ዋጋ ከፍ ይላል። በጥሩ ሁኔታ ዝግጁ ሆነው ተጨማሪ ጥገና የማያስፈልጋቸው ቤቶች የበለጠ ኪራይ ዋጋ እና ተፈላጊነት ይኖራቸዋል። ቤቶቹ ያለባቸው ተጨማሪ ወርሃዊ ወጪዎች: ( Condo fee )እራሱ ተከራዮች ቤቱን ለማከራየት እደአንድ መስፈርት የሚያዩት ጉዳይ ነው። አብዛኛውን ግዜ የነዋሪው ቁጥር ዝቅ ያለባቸው አፓርትመንት / ቤቶች አንስቶ ብዙ ነዋሪ ያለባቸው ህንፃዎች በወር የሚከፍሉት ወራዊ መዋጮ 3ሺ አንስቶ እስከ 5ሺ ድረስ ይደርሳል።  ከበጋ ወራት ላይ ብዙ የስራ እና ትምህርት እንቅስቃሴዎች ስለሚኖሩ ከክረምቱ ጊዜ በተሻለ መልኩ የኪራይ ፍላጎቶች ይኖራሉ። በተመሳሳይ አካባቤ ያሉ ቤቶችን የኪራይ ዋጋ ማጥናት ከዛም በመነሳት የቤቶቻችን የኪራይ ዋጋ መተመን ቶሎ ቤታችንን ለማከራየት ይረዳናል። የጥሩ የኢንቨስተር ባህሪም ነው!


Related Articles

Discover more insights and stories

Sell Your Property